Sunday, October 6, 2024
spot_img

‹‹የከተማው መናኝ›› የተሰኘ መጽሐፍ ለአንባቢያን ሊቀርብ ነው

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ግንቦት 4፣ 2013 ― ‹‹የከተማው መናኝ›› የሚል ርእስ ያለው አዲስ መጽሐፍ ለአንባቢያን ሊቀርብ ነው፡፡ በእውቁ የሙዚቃ አቀናባሪ፣ ገጣሚ፣ ዜማ ደራሲ እና ፕሮዲዩሰር ኤልያስ መልካ ሥራዎች ላይ የሚያተኩረው ይህ መጽሐፍ፣ የተሰናዳው በጋዜጠኛ ይነገር ጌታቸው ነው፡፡

የመጀመሪያዎቹን የቅንብር ሥራዎቹን ካስደመጠበት ከ1990ዎቹ መጀመሪያ አንስቶ ለ18 ገደማ ዓመታት ከ40 በላይ አልበሞች እና ከ400 በላይ ሙዚቃዎች መሥራቱ የሚነገርለት ኤልያስ መልካ፣ በሞያው የትውልዱ ቁንጮ እንደሆነ በራሱ ዘመን ተጋሪዎች የሚመሰከርለት ነው፡፡

የሙዚቃ አቀናባሪ፣ ጊታሪስት፣ የዜማ እና ግጥም ደራሲው ኤልያስ መልካ በ42 ዓመት እድሜው ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው መስከረም 23፣ 2012 ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img