አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ግንቦት 3፣ 2013 ― ትግራይ ቴሌቪዥን ውስጥ ለሚሰሩ ጋዜጠኞችና ባለሙያዎች የድህረ ግጭት አዘጋገብ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡
በዛሬው እለት በአዳማ ከተማ እየተሰጠ የሚገኘውን ሥልጠና የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን፣ የሰላም ሚንስትርና ሌሎች ድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች በቅንጅት አዘጋጅተውታል ተብሏል፡፡ ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የተውጣጡ መምህራን፣ የሰላም ሚንስትር ያዘጋጃቸው የግጭት አፈታት ባለሙያዎች፣ የስነ-ልቡና ባለሙያዎች ስልጠናውን በስጠት እንደሚሳተፉበትም ነው አዲስ ዘይቤ ድረ ገጽ የዘገበው፡፡
የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ ኢድሪስ እንደተናገሩት የሥልጠናው ትኩረት ጋዜጠኞች በሰላም ግንባታ ላይ ስለሚኖራቸው ሚና፣ ጫናን ተቋቁመው ለሕዝብ የሚጠቅሙ መረጃዎችን ማሰራጨት ስለሚችሉበት መንገድ፣ የመረጃን ትክክለኛነት ማጣራት ስለሚቻልባቸው መንገዶች ትኩረት ያደረገ ነው፡፡
የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የትግራይ ቴሌቪዥንን ጨምሮ በክልሉ የሚገኙ የማኅበረሰብ ሬዲዮዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ እንዲመለሱ ድጋፍ ያደርጋልም ብለዋል ዳይሬክተሩ።