Sunday, November 24, 2024
spot_img

ለቴሌኮም ኦፕሬተሮች የወጣው ጨረታ ሊሰረዝ ይችላል ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ግንቦት 3፣ 2013 ― የኢትዮጵያ የኮሚኒኬሽን ባለሥልጣን ሁለት የግል ቴሌኮም ኦፕሬተሮችን ፈቃድ ለመስጠት ባወጣው ጨረታ ሁለት ተጫራቾች ብቻ ብቁ ሆነው በመገኘታቸው አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱ ተነግሯል፡፡

ባለሥልጣኑ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ አሸናፊውን ለማሳወቅ እየተጠበቀ ቢሆንም፣ መንግሥት ይህን ውሳኔውን ሊለውጥ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል።

በጉዳዩ ላይ የገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ የኢኮኖሚ አማካሪ የሆኑት ብሩክ ታየ (ዶ/ር) ‹‹ጨረታው ሊሰረዝ ይችላል፤ አንዱን ተሳታፊ ልንመርጥ ብቻ እንችላለን ወይንም ደግሞ ለሁለቱም ተቋማት የአሸናፊነት ፈቃድ ልንሰጥ እንችላለን።›› ሲሉ ከኢትዮጵያን ቢዝነስ ሪቪው መጽሔት ጋር ባደረጉት ቆይታ መናገራቸውን የመጽሔቱ እህት ጋዜጣ የሆነው አዲስ ማለዳ በድረ ገጹ አስነብቧል፡፡

ባለሥልጣኑ በመላው አገሪቱ የቴሌኮም አገልግሎት ማቅረብ ለሚችሉ ሁለት ተጨማሪ ኩባንያዎች ፈቃድ ለመስጠት ያወጣው ጨረታ ኩባንያዎቹ በተገኙበት ሚያዝያ 18፣ 2013 የጨረታ ሰነዱን መክፈቱ ይታወሳል፡፡

በዚሁ መሠረት ለጨረታ የቀረበውን ሁለት የቴሌኮም አገልግሎት ፈቃድ ለማግኘት የጨረታ ሰነዶቻቸውን ያስገቡት ኩባንያዎች የደቡብ አፍሪካው ኤምቲኤን እና ዓለም አቀፍ ጥምረት ለኢትዮጵያ በሚል መጠሪያ የተመሠረተው የቴሌኮም አገልግሎት ጥምረት ናቸው።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img