Monday, October 7, 2024
spot_img

በአዲስ አበባ ከ300 በላይ ቦታዎች የጸጥታ ስጋት አለባቸው በሚል መለየታቸውን የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ግንቦት 2፣ 2013 ― የከተማው የሰላምና ፀጥታ ቢሮ የጉዳዮች አፈታትና መረጃ ዳይሬክተር አቶ ማስረሻ ሀብቴ ለሸገር እንደነገሩት በከተማው የጸጥታ ስጋት አለባቸው ተብለው የተለዩት 312 ቦታዎች ናቸው፡፡

በሁሉም ክፍለ ከተሞች ውስጥ በሚገኙ 44 ወረዳዎች ይገኛሉ የተባሉት ቦታዎቹ፣ የሁሉንም ትኩረት የሚሹ በመሆናቸው የተለዩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

እነዚህ ቦታዎች ከመሬት ወረራ ጋር በተያያዘ፣ የብሔር ግጭት፣ የቡድን ግጭት፣ ከባድ ወንጀል የሚጸምባቸው፣ የቡድን ጸብ የሚፈጥሩ ያሉባቸው እና ከቤተ እምነቶች ጋር የተገናኙ ናቸው ብለዋል፡፡

ከ200 በላይ የምርጫ ጣቢያዎች የጸጥታ ስጋት ሊኖርባቸው ይችላል ተብለው መለየታቸውን የገለጹ ኃላፊው፣ የነዚህ ሁኔታ ደረጃው በጣም ከፍተኛ ነው ላይባል ይችላል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img