Saturday, November 23, 2024
spot_img

የአቡነ ማትያስ መግለጫ የግላቸው እንጂ የሲኖዶሱ አቋም አይደለም ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ግንቦት 2፣ 2013 ― የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊና እንዲሁም ሲዳማና የጌዲዮ ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ ብጹዕ ወ ቅዱስ አቡነ ማቲያስ ከሰሞኑ የሰጡት መግለጫ የግላቸው እንጂ የቅዱስ ሲኖዶስ ወይም የቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዳልሆነመ ገልጸዋል፡፡

ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ መሰል መግለጫዎች የሚሰጡት የምዕላተ ጉባኤውን እና የቋሚ ሲኖዶሱን አዎንታ ሲያገኙ መሆኑን ያስታወሱ ሲሆን፣ ‹‹ቅዱስ ሲኖዶስ እና ቋሚ ሲኖዶስ ሳይወስን ቅዱስ ፓትሪያርኩ በግላቸው ቤተክርስቲያን እና ቅዱስ ሲኖዶስን ወክለው መግለጫ መስጠት አይችሉም›› ብለዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ በቀጣዩ ርክበካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ በአጀንዳ የሚነጋገርበት መሆኑንም ጭምር አስረድተዋል።

‹‹ቅዱስ ፓትሪያርኩ የሰጡት መግለጫ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ያለመሆኑን እየገለጽን፣ ይህንንም የዓለም መንግሥታት በሃገር ውስጥ እና በውጭ ያላችሁ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግሥት ሊያውቁት እና ሊገነዘቡት ይገባል›› ብለዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን መሪ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ባሳለፍነው ቅዳሜ በወጣ የቪድዮ ንግግራቸው ስለ ትግራይ ክልል እንዳልናገር ‹‹ድምጼ ታፍኗል›› ማለታቸው ይታወሳል። በትግራይ ክልል የሚካሄደውን ግጭት ‹‹የአረማዊነት ሥራ›› በማለት የጠሩት ፓትርያርኩ፤ ዓለም አቀፍ መንግሥታት የንፁሐን ግድያ የሚቆምበትን መንገድ እንዲፈልጉ ተማጽኖአቸውን አቅርበው ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img