Monday, October 7, 2024
spot_img

ወይዘሪት ብርቱካን በመጪው ምርጫ ላይ ጥያቄ ላነሱት ለአምስቱ የአሜሪካ ሴናተሮች ምላሽ ሰጡ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ግንቦት 2፣ 2013 ― የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሊቀመንበር ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ከቀናት በፊት በመጪው ወር የሚካሄደው ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ አሁን ባለበት ሁኔታ ነጻ፣ ሚዛናዊ እና ግልጽ ሆኖ ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን አያሟላም በማለት በጆ ባደን አስተዳደር የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ ሆነው ለተሾሙት አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ደብዳቤ ለጻፉት አምስት የአሜሪካ ሴናተሮች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ወይዘሪት ብርቱካን በምላሻቸው በቅድሚያ የአሜሪካ መንግሥት ምርጫ ቦርድ ላካሄዳቸው የተሃድሶ እና በተቋ ግንባታ ሥራዎች ላይ በዩኤስአይዲ በኩል ድጋፍ ሲደርግ መቆየቱን አንስተው አሞግሰዋል፡፡

በሌላ በኩል ከሰሞኑ ሴናተሮቹ ምርጫው አሁን ባለበት ሁኔታ ነጻ፣ ሚዛናዊ እና ግልጽ ሆኖ ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን አያሟላም ለማለታቸው ግን ምርጫ ቦርድ አከናውኖዋቸዋል ያሏቸውን ጉዳዮች ዘርዝረዋል፡፡

ከነዚህ መካከል ለምርጫ ተአማኒነት ማረጋገጫ ናቸው ያሉትን የባለ ድርሻ አካላት ተሳትፎ በመጥቀስ፣ በአሁኑ ወቅት በቦርዱ ከተመዘገቡ 49 ፓርቲዎች መካከል 46 የሚሆኑት በምርጫው ለመሳተፍ እጩዎች አስመዝግበዋል ያሉ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በምርጫው ሪከርድ የሆነ ከ9 ሺሕ በላይ እጩዎች ተሳታፊ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡

ወይዘሪት ብርቱካን ጨምረውም ምርጫው ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን እንዲያሟላ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችም መዘጋጀታቸውን እንዲሁም ሌሎችንም ጉዳዮች አንስተዋል፡፡

ከቀናት በፊት በተመሳሳይ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ ምላሽ መስጠታቸው መነገሩ የሚታወስ ነው፡፡

መጪው አገራዊ ምርጫ ላይ ጥያቄ በማንሳት ደብዳቤውን የጻፉት ሴናተሮቹ ቤንጃሚን ኤል ካርዲን፣ ቲም ኬይን፣ ጃኪ ሮስን፣ ኮርይ ኤ ቡከር እና ጄ ማርኬይ ነበሩ፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img