Monday, October 7, 2024
spot_img

ኦቢኤን ባልደረባው ጋዜጠኛ ሲሳይ ፊዳ በሸኔ በታጣቂዎች እንደተገደለበት አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ግንቦት 2፣ 2013 ― የኦሮሞ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (ኦቢኤን) ጋዜጠኛ ሲሳይ ፊዳ ትላንት 11 ሰአት ከ30 ላይ ከሰርግ ሲመለስ በመኖሪያ ቤቱ አካባቢ በሁለት የሸኔ ታጣቂዎች የግድያ ወንጀሉ መፈፀሙን በቄለም ወለጋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የአካባቢ ሰላም አስከባሪ ምክትል ዳሬክተር ኢንስፔክተር አሕመድ ያሲን ነግረውኛል ብሎ የሚሠራበት ጣቢያ ዘግቧል፡፡

የወንጀሉ ፈፃሚዎች ማንነት እንደተደረሰበት እና በቅርብ ክትልል እየተደረገ መሆኑን ኢንፔክተሩ ገልፀዋል፡፡

ሲሳይ ፊዳ መልካም ሥነ ምግባር ያለው እና ለሕዝብ ሐቅ በትጋት የሚሠራ ጠንካራ ጋዜጠኛ ነበር ያለው ኦቢኤን፣ ለቤተሰቦቹ መጽናናትን ተመኝቷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img