Monday, October 7, 2024
spot_img

ኢትዮጵያ ከዓለማችን ግዙፍ የወደብ አንቀሳቃሾች መካከል ከሆነው ዲፒ ዎርልድ ጋር ስምምነት ፈጸመች

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሚያዝያ 30፣ 2013 ― የኢትዮጵያ መንግሥት የዩናይትድ አራብ ኤሜሬትስ ንብረት ከሆነው ዲፒ ዎርልድ ጋር የተፈራረመው ስምምነት ኢትዮጵያን ከሶማሊላንዱ በርበራ ወደብ ጋር ለማገናኘት የሚያስችል ነው ተብሏል።

የአቡ ዳቢ ዕድገት ፈንድና የዩናይትድ ኪንግደም ዓለም አቀፍ ዕድገት በትብብር የሚገነቡት የወደቡ ፕሮጀክት፣ ከራስ ገዟ የሶማሊላንድ በርበራ ወደብ ሁለቱን ሃገራት እስከሚያገናኘው የዋጃሌ ከተማ ድረስ የሚዘረጋ ነው፡፡

ዲፒ ዎርልድ ከኢትዮጵያ ጋር በተገባው ውል ውል መሠረት ዕቃ አስመጪና ላኪ ድርጅቶች በጥምረት እንዲሰሩ ያስችላል የሚል ሲሆን፣ ድርጅቱ 1 ቢሊዮን ዶላር አፍስሶ ደረቅ ወደብ፣ ጎተራ፣ መጋዘን እንዲሁም ማቀዝቀዣ የተገጠመላቸው ማከማቸዎች ለመገንባት አቅዷል።

ስምምነቱን አመልክቶ የተናገሩት የዲፒ ዎርልድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሱልጣን አሕመድ ቢን ሱሌይማን ስምምነቱ በርካታ ሥራዎች የሚፈጥር፣ አዳዲስ ቢዝነሶችና ኢንቨስተመንቶች ወደ ኮሪደሩ እንዲመጡ የሚያስችል እና አልፎም ሃገሪቱ ከዓለም አቀፍ ንግድ ጋር ያላትን ግንኙነት እንደሚያጠናክር ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል በስምምነቱ ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ዳግማዊት ሞገስ ኢትዮጵያ ‹‹የወደብ መንገዶቿን የተሰባጠረ ለማድረግና ዕቃና አገልግሎት የሚመላለስበትን አማራጭ ለማስፋት እየሠራች ነው›› ሲሉ መናገራቸውንም ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በፈረንጆቹ 2016 ሶማሊላንድ ዲፒ ዎርልድን ቀጥራ ወደቧን ሰፋ አድርጎ እንዲገናባላት የ30 ዓመት ስምምነት መፈራረሙ አይዘነጋም። በወቅቱ በየብስ የተከበበችው ኢትዮጵያ ከፕሮጀክቱ 19 በመቶ ድርሻ የተጋራች ሲሆን፣ 30 በመቶው ድርሻ የተያዘው በሶማሊላንድ ሲሆን የተቀረው 51 በመቶ ድርሻ የዲፒ ወርልድ ነው።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img