Sunday, September 22, 2024
spot_img

የአውሮፓ ኅብረት ለምርጫው የባለሙያዎች ቡድን እንደሚልክ ማስታወቁን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለጹ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሚያዝያ 30፣ 2013 ― የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓ ኅብረት ለመጪው ምርጫ ታዛቢዎችን እንደማይልክ ቢገልጽም፣ የባለሙያዎች ቡድን እንደሚልክ ማስታወቁን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል፡፡

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በኢትዮጵያ በመጪው ወር የሚካሄደውን አገራዊ ወር ምርጫ ላይ የሚታዘቡ አካላትንም ይፋ አድርገዋል፡፡

ቃል አቀባዩ በዛሬው መግለጫቸው የአሜሪካ ኤምባሲ እና የብሪቲሽ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች፣ የሩሲያ ሲቪል ማኅበረሰብ፣ የአፍሪካ ኅብረት፣ የምሥራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ብርጌድ ቲም፣ መቀመጫቸውን አሜሪካ ያደረጉና ናሽናል ዴሞክራሲ እና ኢሎክቶራል ኢንስቲትዩት ፎር ሰስቴኔብል ዴሞክራሲ ኢን አፍሪካ የተባሉ ተቋማት ምርጫውን እንደሚታዘቡ ገልጸዋል፡፡

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በመግለጫቸው የግንቦቱ ምርጫ ‹‹በሀገሪቱ የምርጫ ታሪክ ዴሞክራሲያዊ ይሆናል›› ብለዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img