Sunday, September 22, 2024
spot_img

የአውሮፓ ኅብረት ምርጫውን አልታዘብም ያለበትን ውሳኔ መልሶ እንዲያጤነው ተጠየቀ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሚያዝያ 30፣ 2013 ― የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ ላለመታዘብ ያስተላለፈውን ውሳኔ መልሶ እንዲያጤነው የጠየቀው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ነው፡፡

ምክር ቤቱ በሰጠው መግለጫ የአውሮፓ ኅብረት እስካሁን የተደረጉትን የይስሙላ ምርጫዎችን ሲታዘብ ሰንብቶ በዘንድሮው ምርጫ ከታዛቢነት ለመውጣት የወሰነበትን ምክንያት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሊያሳውቅ ይገባል ነው ያለው፡፡

የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያ የሚደረገውን ምርጫ እንዲታዘብ ጥልቅ ፍላጎት እንዳለው የገለጸው ምክር ቤቱ፣ ኅብረቱ ምርጫውን ላለመታዘብ የያዘውን አቋም በድጋሚ ተመልክቶ ታዛቢዎቹን እንዲልክ አሳስቧል።

የኢትዮጵያ መንግሥትም አሁን የያዘውን አቋም ከዓለም አቀፍ የምርጫ ታዛቢነት ሕጎች ጋር በማገናዘብ፣ ጉዳዩን መልሶ በድርድር እንዲመለከተው ጥሪ ያቀረበው ምክር ቤቱ፣ ድርድሩ መደረግ ያለበትም የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በማይጻረር መልኩ መሆኑንም አክሏል።

የአውሮፓ ኅብረት ባለፈው ሰኞ ባወጣው መግለጫ በመጪው ግንቦት ወር በኢትዮጵያ በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ታዛቢዎችን ለመላክ የያዘውን እቅድ መሰረዙን አስታውቆ ነበር። ኅብረቱ እቅዱን የሰረዘው የምርጫ ታዛቢዎችን ለመላክ በቁልፍ መለኪያዎች ረገድ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ባለመስማማቱ መሆኑን መግለጹ መነገሩ የሚታወስ ነው፡፡

ውሳኔውን በተመለከተ የኢትዮጵያን አቋም በዚህ ሳምንት የተናሩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቃባይ ዲና ሙፍቲ፣ ህብረቱ ምርጫውን ላለመታዘብ በምክንያቶች የጠቀሳቸው ጉዳዮች ‹‹የኢትዮጵያን ነጻነት፣ ሉዓላዊነት እና ደህንነት የሚጻረር ነው›› ብለውታል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img