Saturday, November 23, 2024
spot_img

የዓለም ጤና ድርጅት ለቻይናው ሲኖፋርም ክትባት እውቅና ሰጠ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሚያዝያ 30፣ 2013 ― የዓለም ጤና ድርጅት የቻይናውን የሲኖፋርም ክትባት ‹‹ደህንነት፣ ውጤታማነት እና ጥራት›› ማረጋገጡን በትላትናው እለት አሳውቋል፡፡

የክትባቱ ፈቃድ ማግኘት ‹‹የጤና ሠራተኞችን እና ለአደጋ የተጋለጡ ዜጎችን ለመከላከል የሚያስፈልገውን የኮቪድ-19 ክትባት ተደራሽነት የማፋጠን አቅም አለው›› ያለው ዓለም አቀፉ የጤና ተቋም፣ ክትባቱ ዕድሜያቸው 18 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሰዎች በሁለት ዙር እንዲሰጥ መክሯል፡፡

ይህንኑ ተከትሎም የሲኖፋርም ክትባት በድርጅት ይሁንታ ያገኘ ከምዕራባውያን ውጭ የተሠራ የመጀመሪያ ክትባት ሆኗል፡፡

ከዚህ ቀደም ለፋይዘር፣ የአስትራዜኔካ፣ የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን እና ሞደርና ክትባቶችን እቅና የሠጠው ድርጅቱ፣ ለሌላኛው ቻይና ሠራሽ ክትባት ሲኖቫክ በሚቀጥሉት ቀናት ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ የሩሲያ ስፑትኒክም በግምገማ ላይ ይገኛል፡፡

ሲኖፋርም የዓለም ጤና ድርጅት ዕውቅና ከመስጠቱ በፊትም ቢሆን በግምት 65 ሚሊዮን ዶዝ መሰጠቱን መረጃዎች የሚያመለክቱ ሲሆን፣ ከቻይና በተጨማሪ ክትባቱን ኤምሬትስ፣ ፓኪስታን እና ሃንጋሪ እየተጠቀሙበት እንደሚገኙ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የሲኖፋርም ክትባት ምልክት ላሳዩ እና ታምመው ሆስፒታል ለገቡት ውጤታማነቱ 79 በመቶ እንደሆነ ተገምቷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img