Sunday, November 24, 2024
spot_img

በኢትዮጵያ የታቀደው ዲሞክራሲያዊ ሽግግር እንዳበቃለት በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ምክትል ልዩ መልክተኛ ተናገሩ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሚያዝያ 29፣ 2013 ― የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪቃ ቀንድ ጉዳዮች ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፊልትማን ምክትል ተደርገው የተሾሙት ፔይተን ክኖፕፍ በኢትዮጵያ የታቀደው ዲሞክራሲያዊ ሽግግር እንዳበቃለት ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ ጀምሮ የኢትዮጵያ የፖለቲካ እና ደኅንነት ጉዳይ ከመሠረቱ መቀየሩን የገለጹት ምክትል ልዩ መልክተኛው፣ በመሆኑም በቀጣይ በአገሪቱ ሁሉን ያካተተ ውይይት ማድረግ የግድ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

ምክትል ኃላፊው ጨምረውም እነሱ ከሚፈልጉት ተቃራኒ ባለፉት ጊዜያት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ተቃዋሚዎች የነበሩ ፖለቲከኞች በሙሉ መታሰራቸውንም ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል በቅርቡ በኦሮሞ እና በአማራ የፖለቲካ መሪዎች መካከል ንግግር መደረጉን እንደ በጎ ያነሱት ምክትል ልዩ መልክተኛው፣ በቀጣይም ሁሉንም ያካተተ ውይይት ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

አሜሪካ በቅርቡ በምሥራቅ አፍሪካ መፍትሔ ብላ የሾመቻቸው ልዩ መልእክተኞች እንዲፈቷቸው ከምትፈልጋቸው ችግሮች መካከል የትግራይን ግጭት ጨምሮ በቅጡ ያልረጋውን የኢትዮጵያ ሁኔታ፣ በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል እየተባባሰ የመጣው ውጥረት እና የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ውዝግብ ይገኙበታል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img