አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሚያዝያ 29፣ 2013 ― መንግሥት ከዚህ በኋላ ከትግራይ ክልል አጠቃላይ የቆዳ ስፋት ውስጥ በ14 በመቶው ብቻ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡ ቀሪው 86 በመቶው የዓለም ምግብ ፕሮግራምን ጨምሮ በሌሎች ዓለም አቀፍ እርዳታ ሰጭ ተቋማት እንደሚሸፈን ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ ገልጸዋል፡፡
ፍቃድ ያገኙ የረድኤት ተቋማት ኢሜይል በመላክ ብቻ ድጋፎችን ለማቅረብ እና ሠራተኞቻቸውም ለመንቀሳቀስ ይችላሉ ነው የተባለ ሲሆን፣ ሰብዓዊ ድጋፎችን ለማድረግ አልተቻለም በሚል የሚቀርቡ ክሶችና ወቀሳዎች ከአሁን በኋላ ተቀባይነት እንደሌላቸውም ተገልጿል።
በሌላ በኩል ኮሚሽነሩ በክልሉ በረሃብ ሰበብ የሞቱ ሰዎችን በሚመለከትም ‹‹በረሀብ የሞተ ሰው የለም›› ሲሉ መልሰዋል፡፡ ሆኖም ዓለም አቀፍ ተቋማት ‹‹እርዳታ ለማግኘት ሲሉ ጉዳዩን እያስጮሁት›› እንደሆነ ተናግረዋል፡፡