Sunday, September 22, 2024
spot_img

የአሜሪካው ልዩ መልእክተኛ ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር ተወያዩ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሚያዝያ 29፣ 2013 ― የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪቃ ቀንድ ጉዳዮች ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፊልትማን አስመራ ተገኝተው ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር መወያየታቸው ተሰምቷል፡፡

በደንደን ማረፊያ ተደርጓል በተባለው ውይይት አራት ሰአታት የፈጀ እንደነበር የአገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

በውይይቱ ላይ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ከአሜሪካ ጋር በትብብር የምሥራቅ አፍሪካ ችግሮችን ለመፍታት እንደምትሠራ ዝግጁ መሆኗ ተናግረዋል ያሉት የማነ፣ የአሜሪካው መልእክተኛም በቀጣናው ያለው ችግር እንዲፈታ አገራቸው ያላትን ፍላጎት እንደገለጹ አስፍረዋል፡፡

ባለፉት ቀናት ካይሮ የነበሩት ጄፍሪ ፊልትማን፣ ሱዳን እና ኢትዮጵያም ቀጣይ መዳረሻቸው መሆኑ ተነግሯል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img