Monday, October 7, 2024
spot_img

አሜሪካ በቻይና ተወንጭፎ ከቁጥጥር ውጭ ሆኗል ለተባለው ሮኬት ኃላፊነት እንዲወሰድ ጠየቀች

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሚያዝያ 28፣ 2013 ― አሜሪካ ባለፈው ሳምንት በቻይና ተወንጭፎ ከቁጥጥር ውጭ በመውጣቱ በአሜሪካ መከላከያ ኃይል በመጪው ቅዳሜ ወደ መሬት ተመልሶ ሊከሰከስ ይችላል ተብሎ በተገመተ ሮኬት ዙሪያ ኃላፊነት መውሰድ እንደሚገባ ጠይቃለች፡፡

የቻይና ስፔስ ኤጀንሲ የተወነጨፈው ሮኬት ከቁጥጥር ውጭ መውጣት አለመውጣቱ ላይ እስካሁን ያለው ነገር ባይኖርም፣ አገሩን በሚመራው የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የሚታተመው ግሎባል ታይምስ የተባለ ጋዜጣ የተወነጨፈው ሮኬት ቀላልና በከባቢ አየር ላይ ፈንድቶ ሊቀር የሚችል መሆኑን በመግለጽ በሰው ላይ ጉዳት የማድረስ እድሉ አነስተኛ መሆኑን አስነብቧል፡፡

ጋዜጣው ይህን ቢልም በአሜሪካው የሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ አስትሮፊዚስት የሆኑት ጆናታን ማክዶዌል በበኩላቸው አሁንም ቢሆን በሰዎች መኖሪያ አካባቢዎች ላይ ስብርባሪው የመውደቅ እድል ያለው መሆኑን የገለጹ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ቻይና ያስወነጨፈችው ስብርባሪ ብረቶች በአይቮሪኮስት በርካታ ሕንጻዎችን ማውደሙን ማስታወሳቸውን ዘ ጋርዲያን ዘግቧል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img