Monday, October 7, 2024
spot_img

የቡድን ሰባት አገራት አሁንም በትግራይ ያለው ሁኔታ እንደሚያሳስባቸው ገለጹ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሚያዝያ 28፣ 2013 ― የቡድን ሰባት አገራት ባደረጉት ስብሰባ ላይ በትግራይ ክልል ቀጥሏል ያሉት ግጭት እና የሰብዓዊ መብትና የሰብዓዊ ድጋፍ ቀውስ በእጅጉ እንደሚያሳስባቸው ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በክልሉ ደርሷል ያሉትን የሰላማዊ ሰዎች ግድያ፣ የሴቶች አስገድዶ መደፈር፣ የወሲባዊ ብዝበዛ እና ሌሎችም ፆታ ላይ የተመሰረቱ ጥቃቶችን ያወገዙ ሲሆን፣ የሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ቅርሶችን መውደም እና መዘረፍ አንስተው በተመሳሳይ አውግዘዋል፡፡

በሌላ በኩል በኢሰመኮ እና በተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር መካከል የተፈፀሙት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማጣራት የተደረገውን ስምምነት በደስታ መቀበላቸውን የገለጹት የቡድን ሰባት አባል አገራት፣ ክልሉ ወደ ቀደመው ሁኔታው እንዲመለስ ሁሉም ወገኖች በፍጥነት ግጭት እንዲያቆሙ፣ የዜጎችን ደህንነት እንዲያረጋግጡ፣ የሰብዓዊ መብቶችንና ዓለም አቀፍ ሕጎችንና የሚዲያ ነፃነት እንዲሁም ተደራሽነትን ያክብሩ ብለዋል፡፡

አክለውም የውጭ ሀይሎች በትግራይ መኖራቸውን እጅግ የሚረብሽና መረጋጋት የሚያሳጣ መሆኑን በመግለጽ፣ የኤርትራ ኃይሎችን ከትግራይ ለማስወጣት የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መንግስታት የሰጡትን መግለጫ ቢቀበሉም፣ ነገር ግን ማስወጣቱ ገና አለመጀመሩ እንዳሰጋቸው ነው የገለጹት፡፡

በትግራይ ክልል ሁሉን አቀፍ ግልፅ የሆነ የፖለቲካ ሂደት እንዲፈጠር ጥሪ ያቀረቡት የቡድን ሰባት አገራት፣ በኢትዮጵያ ተአማኒ ምርጫና ብሔራዊ እርቅ እንዲኖር ለማስቻል ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ሂደት እንዲኖር በተመሳሳይ ጥሪ አቅርበዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img