Sunday, September 22, 2024
spot_img

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ የሱዳን ጉብኝታቸውን አጠናቀቁ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሚያዝያ 28፣ 2013 ― የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ በሱዳን ካርቱም ያደረጉትን የሁለት ቀናት ጉብኝታቸውን አጠናቀው ዛሬ ረፋድ ወደ አሥመራ ተመልሰዋል።

የፕሬዝደንት ኢሳይያስ ጉብኝት በተመረጡ መስኮች የሱዳን እና ኤርትራ ሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር ላይ ማተኮሩን የገለጹት የአገሪቱ የማስታወቂያ ሚንስትሩ የማነ ገብረመስቀል፣ የሥራ ጉብኝቱን ‹‹ስኬታማ የነበረ ነው›› ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

ፕሬዝደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ ዑስማን ሳላህ እና አማካሪያቸውን የማነ ገብረአብን አስክለው ነበር ወደ ሱዳን ያቀኑት፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img