Sunday, October 6, 2024
spot_img

የአሜሪካው አዲስ መልእክተኛ ከግብጽ ፕሬዝዳንት ጋር በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ መወያታቸው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሚያዝያ 28፣ 2013 ― የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪቃ ቀንድ ጉዳዮች ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፊልትማን ካይሮ ተገኝተው ከግብጹ ፕሬዝዳንት ዐብዱልፈታሕ አል ሲሲ ጋር በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ መወያየታቸው ተሰምቷል፡፡

ከትላንት በስትያ ካይሮ የደረሱት ፌልትማን፣ ከፕሬዝዳንት ዐብዱልፈታሕ አል ሲሲ በተጨማሪ የአገሩቱን የውጭ እና የመስኖ ሚኒስትሮችም ማነጋገራቸውን የአሶሽትድ ፕሬስ ዘገባ ያመለክታል፡፡ ጄፍሪ ፊልትማን ከግብጽ ባለሥልጣናት ጋር የተነጋገሯቸው ጉዳዮች ላይ ዝረዝር መረጃ አልወጣም፡፡

አዲሱ የአሜሪካ ልዩ መልእክተኛ የመጀመሪያ ዙር ነው በተባለ ጉዟቸው ከግብጽ ተጨማሪ በኢትዮጵያ፣ በኤርትራ እና በሱዳን ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተጠብቋል፡፡

በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከሕዳሴ ግድብ በተጨማሪ በትግራይ የተነሳውን ጦርነት ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ ዘልቀው እስካሁን እንዳልወጡ የሚነገረውን የኤርትራ ወታደሮችን በሚመለከት ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ይወያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img