Saturday, November 23, 2024
spot_img

በትግራይ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን የድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን በሪፖርቱ አመለከተ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሚያዝያ 28፣ 2013 ― የዓለም አቀፉ ድንበር የለሽ ሐኪሞች ቡድን ሪፖርት በትግራይ ክልል በከፍተኛ ሁኔታ በምግብ እጥረት የተጎዱ ታዳጊዎችን ማግኘቱን በትላንትናው እለት ባወጣው ወቅታዊ ሪፖርት አመልክቷል፡፡

ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን ከቦታ ቦታ ቢለያይም በትግራይ ክልል አብዛኛዎቹ አካባቢዎች የከፋ የምግብ እጥረት እንደሚታይ የገለጸ ሲሆን፣ አብዛኛዎቹ ቤተሰቦች ይመገቡታል ያለው ዳቦ በቀን አንድ ጊዜ እንደሚሰጥ ነው ያመለከተው፡፡

የምግብ እጥረቱ በተለይ በክልሉ ገጠራማ ሥፍራዎች እንደሚታይ ያመለከተው የሐኪሞች ቡድኑ፣ ይኸው ችግር ተከስቶባቸዋል ካላቸው ቦታዎች መካከል የሽረን እና የሽራሮን ገጠራማ ሥፍራዎች ጠቅሷል፡፡

ቡድኑ ጨምሮም በአካባቢው የዝናቡ ወቅት እየደረሰ ሲመጣ የሚካሄደው ጦርነት ገበሬዎችን ወደ ማሳቸው ከመሄድ በመከልከል ሁኔታቸውን ይበልጥ አስከፊ ሊያደርገው እንደሚችልም ነው የገለጸው፡፡

በሌላ በኩል የሐኪሞች ቡድኑ በክልሉ ገጠራማ ሥፍራዎች የሚገኙ የሕክምና ጣቢያዎችን ሁኔታ በሚመለከተም በሪፖርቱ ላይ አስፍሯል፡፡

ይኸው ቡድን አባሎቼ ደርሰውበታል ያለውን በአክሱም ሰሜናዊ ክፍል ሦስት ሰዓታት ያስጉዛል ያለውን አዲፍታው በተባለ አካባቢ የሚገኙ 10 ሺሕ ሰዎች ከጥቅምት ወር ወዲህ ምንም ዐይነት የጤና አገልግሎች አላገኙም ብሏል፡፡

እንደ የድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን ከሆነ በዚህ አካባቢ የሚገኘው ጤና ጣቢያ በከፊል መውደሙን እንዲሁም መዘፈረፉን የገለጸ ሲሆን፣ በውስጡ የሚገኙ ቁሳቁሳችና ፋይሎችም ወለሉ ላይ ተዘርግፎ ይገኝ እንደነበር አስታውቋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img