Sunday, November 24, 2024
spot_img

ዶ/ር ሙሉ ነጋ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምሕርት ሚኒስትር ዲኤታ ተደርገው ተሾሙ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሚያዝያ 28፣ 2013 ― በትላንትናው እለት በዶክተር አብርሀም በላይ እንደተተኩ የተነገረው ዶክተር ሙሉ ነጋ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምሕርት ሚኒስትር ዲኤታ በመሆን እንደተሾሙ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ አስታውቋል፡፡

ዶክተር ሙሉ ነጋ ለረዥም ዓመታት የትግራይ ክልልን ሲመራ የቆየው ሕወሃት መወገዱን ተከትሎ እንደ አዲስ የተቋቋመውን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን ላለፉት ስድስት ወራት የመሩ ሲሆን፣ ከሥልጣናቸው የለቀቁት በምን ምክንያት እንደሆነ በይፋ የተነገረ ነገር የለም፡፡

ሬውተርስ ትላንት ምሽት ይዞት በወጣው ዘገባም የቀድሞው የክልሉ ሥራ አስፈጻሚ ከሥልጣናቸው የለቀቁት በገዛ ፍቃዳቸው መሆኑን ምክትላቸው አቶ አበበ ገብረሕይወት ይኅደጎ ነግረውኛል ብሏል፡፡ ሆኖም እርሳቸውም ቢሆን የቀድሞ አለቃቸው የለቀቁበት ምክንያት ምን እንደሆነ ግን የገለጹት ነገር የለም።

በተመሳሳይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት የዶክተር አብርሃም በላይን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሹመት አረጋግጧል፡፡

ዶክተር አብርሃም በላይ የሳይንስ እና ኢኖቬሽን ሚኒስቴርን ሲመሩ የቆዩ መሆናቸው የሚታወቅ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img