Sunday, October 6, 2024
spot_img

የኦንላይን ሚዲያዎችን ወደ ሥርዐት ለማስገባት እየሠራ እንደሚገኝ የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሚያዝያ 27፣ 2013 ― አዲሱ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን አመራር የበይነ መረብ (የኦንላይን) መገናኛ ብዙኃንን ለመመዝገብ፣ ለመደገፍና ወደ ሥርዓት ለማስገባት የመጀመሪያው ትኩረቱ አድርጎ እየሠራ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

በቅርቡ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት አቶ መሐመድ እድሪስ ነግረውኛል ብሎ ለሪፖርተር እንዳስነበበው፣ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን ከዚህ በፊት ክትትልና ቁጥጥር አይደረግበትም ነበር፡፡ ሆኖም መሥሪያ ቤታቸው እንደ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ሆኖ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ የመጀመሪያው ቁልፍ ተግባር አድርጎ የያዘው ጉዳይ፣ ዘርፉን መመዝገብና ወደ ትክክለኛው ሥርዓት ማስገባት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ተቋሙ የተሰጠውን ተልዕኮ መመለስ በሚችልበት ቁመና ላይ እንዲገኝ የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ያስታወቁት ዋና ዳይሬክተሩ፣ በዚህም በዓቃቤ ሕግ ሥር ባለ ገለልተኛ የባለሙያዎች ምክር ቤት የተዘጋጁ ስምንት መመርያዎች እንደነበሩና እነዚህን መመርያዎች የማፅደቅና ተግባራዊ የማድረግ ሥራ እንደሚከናወን አስረድተዋል፡፡

እንደ ዳሬክተሩ ከሆነ በአዲሱ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 መሠረት የኢትዮጵያ ዜግነት ያለው ሰው በግል ወይም በድርጅት የበይነ መረብ የመገኛ ብዙኃን ማቋቋም ከፈለገ ባለሥልጣኑ እንዲመዘግበው ማመልከት ይችላል፡፡

ባለሥልጣኑ የምዝገባ ጥያቄው በቀረበለት በ30 ቀናት ውስጥ ምዝገባ በማከናወን የምዝገባ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፡፡ አመልካቹ መሟላት ያለበትን መሥፈርት አሟልቶ ቀርቦ በ30 ቀናት ውስጥ የዕውቅና የምስክር ወረቀት ካልተሰጠው፣ ሕጋዊ ዕውቅና እንዳገኘ ይቆጠራል፡፡

ለምዝገባ ያመለከተ የበይነ መረብ የመገናኛ ብዙኃን ድርጅት መሥፈርቱን አሟልቶ ማመልከቻ ካስገባ 30 ቀናት እስከሚሰጠው መጠበቅ ሳያስፈልገው፣ ወደ ሥራ መግባት እንደሚችልም ገልጸዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img