Sunday, September 22, 2024
spot_img

ፓርላማው ሕወሓትና ኦነግ ሸኔን በአሸባሪነት ለመፈረጅ በቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ላይ ነገ ይወያያል ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሚያዝያ 27፣ 2013 ― የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ሚያዝያ 23፣ 2013 ሕወሓትና ኦነግ ሸኔ የተባሉ ድርጅቶች በአሸባሪነት እንደፈረጁ ባሳለፈው የውሳኔ ሐሳብ ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ ሐሙስ ሚያዝያ 28 ውሳኔ ለመስጠት እንደሚሰበሰብ ተነግሯል፡፡

ምክር ቤቱ ባለፈው ዓመት በወጣው የፀረ ሽብር አዋጅ መሠረት በአሸባሪነት እንዲፈረጅ የውሳኔ ሐሳብ የቀረበበት ድርጅት ወይም ግለሰብ ራሱን የመከላከል መብት እንዲሰጠው የሚደነግገውን አንቀጽን በመጥቀስ፣ የውሳኔ ሐሳብ የቀረበባቸው ድርጅቶች የቀረበውን ውሳኔ ሐሳብ ለማስቀረት ያስችላል ያሏቸውን መከላከያዎች በአካል ቀርበው እንዲያስረዱ የ48 ሰዓት ጊዜ ገደብ መስጠቱን ማሳወቁም አይዘነጋም፡፡

ነገ በሚደረገው ውይይት ምክር ቤቱ የውሳኔ ሐሳቡን ተቀብሎ የሚያፀድቀው ከሆነ፣ መንግሥት በእነዚህ ድርጅቶች ውስጥ በአመራርነትና በአባልነት የሚያገለግሉ ግለሰቦች በአሸባሪነት ለመጠየቅ ያስችለዋል መባሉን የዘገበው ሪፖርተር ጋዜጣ ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የተጠቀሱት ድርጅቶና የድርጅቶቹ አመራሮች ሀብትን ለመውረስ እንዲችል የፀረ ሽብር አዋጅ ይደነግጋል፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ከሳምንታት በፊት መግለጫ ከሕወሓት አመራሮችና ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች የባንክ ሒሳብ ውስጥ የሚገኝ 6 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር እንዲታገድ ማድረጉን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በሕወሓት ባለቤትነት ሥር የነበረውን ኤፈርት የተባለ ኢንዶውመንት ሀብቶች፣ በፌዴራል መንግሥት ሥር በተቋቋመ ባለአደራ አስተዳደር ሥር እንዲተዳደር መወሰኑ አይዘነጋም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img