Friday, November 22, 2024
spot_img

ኢትዮጵያ ችግሮቿን አስወግዳ በሱዳንና ሶማሊያ ሰላም የማስከበር ሥራዋን እንድትቀጥል ማድረግ አሳሳቢ መሆኑን ዴቪድ ሺን ተናገሩ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሚያዝያ 27፣ 2013 ― የቀድሞ በኢትዮጵያና የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉት አምባሳደር ዴቪድ ሺን ይህን ያሉት የአሜሪካ ድምጽ ‹‹አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ እያሳደረች ያለው ጫና ሀገሪቱን ወደ ቻይና ፊቷን እንድታዞር ሊያደጋት ይችላል ወይ›› ብሎ ላቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡

ኢትዮጵያን ወደ ቻይና የመግፋቱ ጉዳይ ‹‹አሳሳቢ›› አለመሆኑን የገለጹት አምባሳደር ሺን፣ በአንጻሩ ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ችግሮች እንዲወገዱ ማድረግና ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካና የምዕራብ ሀገራት አጋር ሆና በሱዳንና ሶማሊያ ሰላም የማስከበር ሥራዋን እንድትቀጥል ማድረጉ›› ይበልጥ አሳሳቢ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዲቪድ ሺን ጨምረውም በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ለሚኖረው ሰላም መስፈን ኢትዮጵያ በጣም አስፈላጊ ሀገር መሆኗን አሜሪካ እንደምታምን አስረግጠው የተናገሩ ሲሆን፣ አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን መልካም ግንኙነት አደጋ ላይ የሚጥል ምንም አይነት እርምጃ መውሰድ እንደማትፈልግ ጠቁመዋል፡፡

ሌላው ለዴቪድ ሺን የቀረበላቸው ጥያቄ የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ ትግራይ ክልል አለመውጣታቸውን ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትስ ከኤርትራ ጋር የሚኖራት ግንኙነት ምን ሊመስል እንደሚችልና በአምባሳደር ጄፈሪ ፌልትማን የሚመራው የአሜሪካ ልዑካን ቡድን ወደ ኤርትራ መጓዙ ምን ሚና ይኖረዋል የሚል ነው።

ዴቪድ ሺን በምላሻቸው አሜሪካ ከዓመታት በኃላ አምባሳደር ፌልትማንን ወደ ኤርትራ መላኳ አበረታች መሆኑን ገልፀው፣ ኤርትራ በትግራይ ክልል ውስጥ ምን እያረገች እንደሆነ በግልፅ ይነጋገራሉ ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

‹‹የኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ ህዝብ የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ መኖራቸውን ይቀበላሉ ብዬ አላስብም›› ያሉት አምባሳደር ሺን፣ ‹‹ይሄ ሉዓላዊነትን የሚፈታተን ነው፤ ስለዚህ ወታደሮቹ በአስቸኳይ ወደ ኤርትራ መመለሳቸው የኢትዮጵያም፣ የአሜሪካም፣ የኤርትራም ፍላጎት ነው። የማይመለሱ ከሆነ ዩናይት ስቴትስ ኤርትራን በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ ተቀባይነት የሌላት ሀገር አርጋ ልትቆጥራት ትችላለች።›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img