አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሚያዝያ 27፣ 2013 ― በኦሮሚያ ክልል የሽግግር አስተዳደር እንዲቋቋም የሚጠይቅ የትዊተር ዘመቻ ሊካሄድ መሆኑን አዘጋጆቹ አስታውቀዋል፡፡
በዛሬው እለት ምሽት ላይ እንደሚካሄድ የተነገረለት የትዊተር ዘመቻ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በክልሉ የሽግግር አስተዳደር እንዲኖር ግፊት እንዲያደርግ የሚጠይቅ ነው ተብሏል፡፡
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት እንደ ሌሎች የአገሪቱ ክልሎች ሁሉ በመጪው ወር የሚካሄደውን አገራዊ ምርጫ የሚያስተናግድ ቢሆንም፣ የትዊተር ዘመቻው አዘጋጆች ግን ምርጫ ሊካሄድ የሚገባው በሰላማዊ ከባቢ ውስጥ መሆን ይገባዋል በሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡
በመሆኑም አሁን የሚካሄደው ምርጫ ቆሞ በብሔሮች መካከል የሰላም ስምምነት እንዲደረግ እንደሚጠይቁም ይናገራሉ፡፡