Saturday, November 23, 2024
spot_img

በጂማ ዞን 30 ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሚያዝያ 27፣ 2013 ― በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በጂማ ዞን ሊሙ ኮሳ ወረዳ ቀጮ ክራክር እና ጋሌ ቀበሌ ማንነት ላይ ያነጣጠረ ነው በተባለ የታጣቂዎች ጥቃት 30 ሰዎች መገደላቸውን ዶይቸ ቨለ የዓይን እማኖች ነግረውኛል ብሎ ዘግቧል፡፡

አረመኔያዊ ነው የተባለው የጅምላ ግድያ የተፈጸመው በጥይት እና በሳንጃ መሆኑንም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

ከ10 ቀናት በፊት ሚያዝያ 15፣ 2013 ደርሷል በተባለው ጥቃት ንጹሐን ዜጎች ላይ ጉዳት መድረሱን ያረጋገጡት የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ጣሒር ኢብራሂም፣ ጥቃቱን ተከትሎ ከአካባቢው ሸሽተው የሄዱ ሰዎችን ለመመለስ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

ከአካባቢው ተፈናቅለው የሄዱ ሰዎች በበኩላቸው አሁን ስጋት እንዳለባቸውና ጥለውት የወጡት ንብረት በሙሉ መዘረፉንም እየገለጹ ይገኛሉ፡፡

በሥፍራው ጥቃት መድረሱን ቀድሞ ይፋ ያደረገው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በአካባቢው የደረሱት የክልል እና የፌዴራል የጸጥታ አካላት ሊደርስ የነበረውን ተጨማሪ ጉዳት መቀነሳቸውን መረዳቱን በመግለጽጽ ሆኖም ወደ ሥፍራው ሠራተኞቹን መላክ እንዳልቻለ አሳውቆ ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img