Sunday, October 6, 2024
spot_img

ኢትዮጵያ በፕሬስ ነጻነት ከ2 ዓመት በፊት ከነበረችበት በ2 ደረጃ ዝቅ አለች

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሚያዝያ 26፣ 2013 ― ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት ኢትዮጵያ በፕሬስ ነጻነት 101ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ አሳውቋል፡፡

ቡድኑ በዛሬው እለት በመከበር ላይ የሚገኘውን የዓለም የፕሬስ ቀን በማስመልከት ባወጣው መረጃ እንዳለው ኢትዮጵያ ከሁለት ዓመት በፊት ከነበረችበት ደረጃ በሁለት ዝቅ ብላለች፡፡

ለ180 ሐገራት ደረጃ የሰጠው ተቋሙ ኖርዌይን ጥሩ የፕሬስ ነጻነት ያለባት ሐገር ሲል በአንደኝነት ሲያስቀምጥ ኤርትራን የመጨረሻ ደረጃ ሰጥቷታል፡፡

የምርመራ ጋዜጠኝነት ለጋዜጠኞች ፈታኝ የሆነባቸው አገራት ደግሞ በኤስያ እና በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ አውሮፓ ሀገራት ናቸው ተብሏል፡፡ ቻይና፣ ቱርክሜንስታን፣ ሰሜን ኮሪያ ደግሞ ኤርትራን አስከትለው ከ177ኛ ጀምሮ ያለውን ደረጃ በመያዝ በመጨረሻዎቹ ረድፍ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

ብሩንዲ በ13፣ ማሊ በ9፣ ሴራልዮን በ10 የቀደመ ደረጃቸውን ካሻሻሉ የአፍሪካ አገራት ናቸው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img