Sunday, October 6, 2024
spot_img

የኮሮናን ሥርጭት ለመቀነስ የተሽከርካሪዎችን የመጫን አቅም እንዲቀንስ ማድረጉን የከተማው ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሚያዝያ 26፣ 2013 ― የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በዛሬው እለት እንዳስታወቀው በከተማው የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመቀነስ የሕዝብ ትራስፖርት የሚሰጡ ተሸከርካሪዎች የመጫን አቅማቸውን እንዲቀንሱ የሚያስገድድ መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡

ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል በተባለው መመሪያ መሠረት፣ ተሽከርካሪዎች የሚቀንሱበት መጠን ይለያይ አንጂ ከታክሲ ውጭ ሁሉም ዐይነት የሕዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች የተሳፋሪ ቁጥር ይቀንሳሉ፡፡

በአዲሱ መመሪያ መሠረት ታክሲዎች በወንበር ሙሉ እና ከኋላ ሦስት ሰው እንዲጭኑ የተቀመጠ ሲሆን፣ ሃይገሮች እና በተለምዶው ቅጥቅጥ የሚባሉት ተሸከርካሪዎች በወንበር ልክና ተራርቀው የሚቆሙ 5 ሰዎች እንዲጭኑ ተብሏል፡፡

በመመሪያው የከተማው አውቶብሶች ደግሞ ከዚህ በፊት ከሚጭኑት በ50 በመቶ ቀንሰው እንዲጭኑ ታዟል፡፡

በነዚህ ተሽካርካሪዎች ላይ የመጫን አቅም ዝቅ ቢደረግም በታሪፍ ላይ የተለየ ጭማሪ እንደማይኖር ቢሮው አሳውቋል፡፡

የመመሪያውን ተፈጻሚነት የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለስልጣንና የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ቢሮ ይቆጣጠራሉ የተባለ ሲሆን፣ ይህን መመሪያ ተላልፈው በሚገኙ አሽከርካሪዎች ላይ ከ500 እስከ 5 ሺሕ የሚደርስ ቅጣት ይጠብቃቸዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img