Saturday, November 23, 2024
spot_img

የአሜሪካ መንግሥት ልዩ መልዕክተኛ ወደ አዲስ አበባ እየመጡ ነው

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሚያዝያ 26፣ 2013 ― የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪቃ ቀንድ ጉዳዮች ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፊልትማን በትግራይ ቀውስና በሌሎች ክፍለ አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ለመምከር ወደ አዲስ አበባ እየመጡ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የተሾሙት ልዩ መልዕክተኛው፣ በትግራይ ያለውን ጦርነት ጨምሮ በታላቁ ሕዳሴ ግድብ እንዲሁም በሱዳንና በኢትዮጵያ የድንበር ውዝግብ ዙሪያ መፍትሔ የማፈላለግ ተልዕኮ የተሰጣቸው ናቸው፡፡

ኢትዮጵያን ጨምሮ በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና አንድ ሳምንት እንደሚቆዩ የተነገረው ፊልትማን፣ በቆይታቸው ከኢትዮጵያ ተጨማሪ ሱዳን፣ ግብፅ እና ኤርትራን ይጎበኛሉ ተብሏል። በአገራቱ በሚኖራቸው ቆይታ ከየሀገራቱ ባለሥልጣናት ጋር የመነጋገር መርሀ ግብር እንዳላቸውም ከአሜሪካ የወጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት የተገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ልዑኩ በትግራዩ ቀውስ ዙሪያ ግጭት ቆሞ ሰላማዊ መፍትሔ እንዲፈለግ እስከ ድርድር የሚደርስ ሐሳብ እንዳላቸው በስፋት እየተነገረ የሚገኝ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ ከአፍሪካ ኅብረትና ከመንግሥታቱ ድርጅት ኃላፊዎች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉም ተገልጧል፡፡

አንጋፋው ዲፕሎማት ጄፍሪ ፊልትማን የመንግሥታቱ ድርጅት የፖለቲካና የፀጥታ አማካሪ በመሆን ሠርተዋል። በመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት በተለይም በሶሪያና ሊባኖስ ጦርነት ቆሞ ሰላም እንዲመጣ በተደረጉ የዲፕሎማሲ ጥረቶች ዋና ልዑክ በመሆን ማገልገላቸውም ይነገርላቸዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img