Sunday, October 6, 2024
spot_img

በቦረና ዞን የድሬ ወረዳ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ተገደሉ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሚያዝያ 25፣ 2013 ― በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ቦረና ዞን ድሬ ወረዳ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ጃርሶ ሀላኬ ትላንት ምሽት ወደ ሦስት ሰአት ገደማ መገደላቸውን አምባ ዲጂታል ከምንጮች ሰምቷል፡፡

በዞኑ በድሬ ወረዳ በሜጋ ከተማ የተገደሉት የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊው፣ በማን እንደተገደሉ እስካሁን ድረስ ከአካባቢው የመንግሥት አካላት በይፋ የተነገረ ነገር የለም፡፡

ግድያውን ተከትሎ የከተማው ሕዝብ ከቤት እንዳይወጣ መደረጉንም ምንጮች ጨምረው ነግረውናል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img