አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሚያዝያ 23፣ 2013 ― የሚንስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሓት) እና “ሸኔ”ን በሽብርተኛ ድርጅትነት እንዲሰየሙ የውሳኔ ሐሳብ ማሳለፉ ተሰምቷል።
ምክር ቤቱ የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው ዐዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀጽ 18 እና 19 መሠረት “ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሓት)” እና “ሸኔ” የሽብር ወንጀልን ዓላማቸው አድርገው የሚንቀሳቀሱ በመሆኑና የድርጅቶቹ የሥራ አመራር ወይም ወሳኔ ሰጭ አካላት ወንጀሉን አምነው የተቀበሉት ወይም አፈጻጸሙን እየመሩት በመሆኑ፤ የሽብር ተግባር መፈጸምም የድርጅቶቹ ጠቅላላ መገለጫ በመሆኑ፤ ድርጅቶቹ በሽብርተኛ ድርጅትነት እንዲሰየሙ ነው የውሳኔ ሐሳብ የተላለፈው።