Sunday, October 6, 2024
spot_img

የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ዛሬ ሌሊት መድፍ እንደሚተኮስ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሚያዝያ 23፣ 2013 ― የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በበዓሉ ዋዜማ ከለሊቱ በ9 ሰዓት ላይ ለዘጠኝ ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ የመከላከያ ሚኒስቴር ኢንዶክትሬሽን ዋና ዳይሬክቶሬት አስታውቋል።

በተጨማሪም የአርበኞች ቀንን ምክንያት በማድረግ የፊታችን ረቡዕ ሚያዚያ 27 2013ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ 21 ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ የመከላከያ ሚኒስቴር ማሳወቁን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡

ይህ በመሆኑም ኅብረተሰቡ ይህንን አውቆ እንዳይደናገጥ እና የጸጥታ አካላትም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ነው የመከላከያ ሚኒስቴር ያሳሰበው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img