Sunday, October 6, 2024
spot_img

የዓለም ጤና ድርጅት የሞደርና የቮቪድ19 ክትባት ለአስቸኳይ ሕክምና አገልግሎት እንዲውል ፈቀደ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሚያዝያ 23፣ 2013 ― የጤና ድርጅቱ በአሜሪካው የመድሃኒት አምራች የተሠራውን የሞደርና የኮቪድ19 ክትባት ለአስቸኳይ ሕክምና አገልግሎት እንዲውል የፈቀደው በትላንትናው እለት መሆኑ ነው የተነገረው፡፡

በጉዳዩ ላይ የተናገሩት የዓለም ጤና ድርጅት ምክትል ዳይሬክተር ማሪያንጌላ ሲማኦ ለቫይረሱን የሚከላከሉ አንዳንድ ክትባቶች ላይ እጥረት ስለሚታይ በርካታ አማራጭ ክትባቶች መኖራቸው አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት የክትባቶችን መኖር የፈለገው በተለይ በብዛት ላኪ የነበረችው ሕንድ በገጠማት የቫይረሱ ፈተና ሰበብ ክትባቶቹን ለጊዜው በማቆሟ ነው ተብሏል፡፡

በትላንትናው እለት በዓለም ጤና ድርጅት ይለፍ ያገኘው ሞደርና የተሰኘው ክትባት አምራች በዚህ ሳምንት እንዳሳወቀው ከሆነ፣ ምርቱን በማስፋት በፈረንጆቹ 2022 እስከ 3 ቢሊዮን ክትባቶችን የማምረት እቅድ እንዳለው አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት አሁን እውቅና የሰጠውን የሞደርናን ክትባት በተመለከተ ባለፈው ጥር ወር የድርጅቱ የበሽታ መከላከል ኤክስፐርቶች ከ18 ዓመት በላይ የሆናቸው ሰዎች ሊወስዱት የሚችሉት እንደሆነ ገልጸው ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img