Saturday, November 23, 2024
spot_img

የኮሮና ክትባት አያስፈልግም ሲሉ የነበሩት ኬንያዊ ዶክተር በቫይረሱ ተጠቅተው ሕይወታቸው አለፈ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሚያዝያ 23፣ 2013 ― በጎረቤት አገር ኬንያ የኮቪድ 19 ክትባት አያስፈልግም በሚል ከሳምንታት በፊት ሲናገሩ ነበር የተባሉት ዶክተር ስቴፈን ካራንጃ በቫይረሱ ተጠቅተው ሕይወታቸው አልፏል፡፡

የኬንያ ካቶሊክ ዶክተሮች ሊቀመንበር የሆኑት ዶክተር ስቴፋን ከሚከተሉት የካቶሊክ ቤተክርስትያን ጋር ከዚሁ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ጋር በተገናኘ ሲነታረኩ መሰንበታቸው ነው የተነገረው፡፡

በተደጋጋሚ በኮቪድ 19 ክትባት ላይ ያነሱ ነበር በተባለው ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ ጥያቄ የአገሪቱ የጤና ባለሥልጣናት እና የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ጭምር ምላሽ መስጠታቸውን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ዶክተሩ ላነሱት ጥያቄ ባለፈው ወር በሰጠው ምላሽ በኬንያ የተሠራጨው ክትባት ከራሱ ከድርጅቱ በተጨማሪ በሌሎች አካላት አስተማማኝነቱ የተረጋገጠ መሆኑን ገልጾ የነበረ ሲሆን፣ በአገሪቱ የሚገኙ የካቶሊክ ቄሶችም ከዶክተር ስቴፋን ካራንጃ በተቃራኒ ክትባቱ ተቀባይነት ያለው ነው ብለውታል፡፡

የኮቪድ 19 ክትባት ሲቃወሙ የቆዩት ዶክተር ስቴፋን ካራንጃ በቫይረሱ ሕይወታቸው ያለፈው ከትላንት በስትያ ሐሙስ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img