Sunday, October 6, 2024
spot_img

በአሜሪካ የግብጽ አምባሳደር በሕዳሴ ግድብ ድርድር ብቸኛዋ ባለ መፍትሔ አሜሪካ ናት አሉ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሚያዝያ 22፣ 2013 ― በአሜሪካ የግብጽ አምባሳደር የሆኑት ሞታዝ ዛህራን ይህንኑ የአገራቸውን አቋም በፎሬን ፖሊሲ ላይ ባስነበቡት ዘለግ ያለ መጣጥፍ ገልጸዋል፡፡

አምባሳደሩ በመጣጥፋቸው የአገራቸው ግብጽን እና ሱዳንን ውሃ ከመሠረቱ የሚያናጋ ነው ያሉትን የሕዳሴ ግድብ ግንባታ በተመለከተ የሚደረገው ድርድር ባለፈው ወር በአፍሪካ ኅብረት መሪነት የተጀመረ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ አሰናክላዋለች ሲሉ ከሰዋል፡፡

ይህ በአገራቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የመጨረሻ እድል የተባለው ድርድር መክሸፉን ተከትሎም፣ ኢትዮጵያ ሁለተኛውን ዙር የግድቡን ሙሌት ለማካሄድ ከጫፍ ላይ እንደምትገኝ በማስታወስ አሁን በድርድሩ ጉዳይ ብቸኛው መፍትሔ ያለው በአሜሪካ እጅ ነው ብለዋል፡፡

አሜሪካ ለጉዳዩ መፍትሔ ማበጀትዋ ቀጣናውን ከብጥብጥ ታድናዋለች ያሉት አምባሳደር ሞታዝ ዛህራን፣ የቀጠናው ሰላም ከደፈረሰ ለሽብርተኝነት መጠቀሚያ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

ይህ እንዳይሆንም የባደን አስተዳደር እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ በዐባይ ወንዝ ላይ የምትገነባውን የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ድርድር አስመልክቶ ግብጽ እና ሱዳን ከሚሉት አሜሪካ እና ሌሎችም ይግቡ አቋም በተለየ ጉዳዩ በአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ብቻ ማለቅ አለበት የሚለውን አቋሟን በተደጋጋሚ ስታሳውቅ መሰንበቷ አይዘነጋም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img