Sunday, October 6, 2024
spot_img

በአጣዬ ከተማ በነበረው የጸጥታ ችግር የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱ መከላከያ ጥሪ ማቅረቡ ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሚያዝያ 22፣ 2013 ― ከጥቂት ቀናት በፊት በአጣዬ ከተማ ተከስቶ የነበረው የጸጥታ ችግር ወደ ሰላምና መረጋጋት በመመለሱ የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱ የኢፌዴሪ መከላከያ ጥሪ ማስተላለፉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

እንደ ዘገባው ከሆነ በአጣዬ ከተማ ተከስቶ የነበረው የጸጥታ ችግር ወደ ሰላምና መረጋጋት መመለሱን የኢፌዴሪ መከላከያ ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ገልጸዋል፡፡

የአገር መከላከያ ሠራዊት ወደ ቀዬአቸው ለሚመለሱ ዜጎች አስፈላጊውን ሁሉ ጥበቃና ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልጧል ነው የተባለው፡፡

በአካባቢው የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ሕዝቡን በማወያየት እያረጋጋ እና ሰላም የማስከበር ስራ በማከናወን ላይ መሆኑም በዘገባው የተመላተ ሲሆን፣ በከተማው በሰውና በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት ተጣርቶ ለሕዝብ ይፋ ይደረጋል ተብሏል፡፡

በአጣዬ ከተማ በነበረው የጸጥታ ችግር ሰበብ በደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋና የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞኖች በሚገኙ ዘጠኝ ወረዳዎችና አምስት ከተሞች በኮማንድ ፖስት ስር መደረጉ የሚታወስ ነው።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img