Saturday, November 23, 2024
spot_img

ኦዳ ፓርቲ ምርጫ ቦርድን በድጋሚ በፍርድ ቤት ረታ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሚያዝያ 22፣ 2013 ― የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ኅብረት (ኦዳ ፓርቲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፓርቲዎች የምዝገባ ሂደት መሰረዙን አስመልክቶ ከዚህ ቀደም በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተወሰነለት ፍርድ በጠቅላይ ፍርድ በተመሳሳይ ጸንቶለታል፡፡

ከዚህ ቀደም ከፍተኛው ፍርድ ቤት ምርጫ ቦርድ ፓርቲውን መሰረዙ አግባቡ አይደለም በሚል ውሳኔ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም፣ ቦርዱ ይግባኝ በማለቱ ጉዳዩ በድጋሚ ሲታይ ነበር፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አንደኛ ፍትሐ ብሄር ችሎት በትላንትናው እለት ሚያዝያ 21 ከሰዓት በኋላ በዋለው ችሎት በተመሳሳይ የከፍተኛ ፍርድ ቤትን ውሳኔ አጽንቶታል።

ፍርድ ቤቱ በውሳኔው ‹‹ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፓርቲውን ለመሰረዝ የሄደበት መንገድ የአስተዳደር አካላት ውሳኔ የመስጠት ስልጣንን ለጥጦ የተጠቀመ፣ የምርጫ ሕጉን ያላከበረና የፓርቲውን አባላት የመደራጀት ሕገ መንግስታዊ መብት የገደበ ነው›› ማለቱን ፓርቲው በገጹ ላይ አሳውቋል፡፡

የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ሕብረት ውሳኔውን ተከትሎ ቀጣይ እርምጃዬን አስመልክቶ ለሕዝቤ እና ለደጋፊዎቼ በቅርቡ መግለጫ እሰጣለሁ ብሏል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img