Sunday, October 6, 2024
spot_img

መከላከያ ከእንግሊዝ አምባሳደር አሊስተር ሚሲፔል ጋር በተገናኘ ለሠራው ዘገባ ይቅርታ ጠየቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሚያዝያ 21፣ 2013 ― የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ ጧት በፌስቡክ “የመከላከያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ በኢትዮጵያ ከእንግሊዝ አምባሳደር አሊስተር ሚሲፔል ጋር ተወያዩ” በሚል ርእስ ላስነበበው ዘገባ ይቅርታ ጠይቋል።

ሚኒስቴሩ “አምባሳደር አሊስተር ከውይይቱ በኋላ እንደተናገሩት፣ አገራቸው ከጎርጎሮሳዊያኑ የዘመን ቀመር ከ2020 ጀምሮ ከአፍሪካ አገራት ጋር እንደ አዲስ ግንኙነቷን አንደምታጠናክር” ተብሎ የተጠቀስነው ከ2018 ጀምሮ በሚል ይስተካከል ብሏል።

በተጨማሪም በዚሁ ዘገባ “በቅርቡ የተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ ለሀገሪቱ የህግ የበላይነት የማረጋገጥ ሒደትና ለቀጣናው ዙሪያ መለስ ሰላምና ደህንነት አስተዋጽኦ ያበረከተ መሆኑን” ተብሎ የተጻፈውም “በትግራይ፣ በሀገሪቱ፣ በቀጣናው እና በሌሎች ጉዳዮች መነጋገራቸውንም አስታውቀዋል” በሚል ተስተካክሎ ይነበብልኝ ሲል አሳውቋል።

የመከላከያ የዘገባ ማስተካከያ የመጣው በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘ የእንግሊዝ ኤምባሲ ዛሬ ከሰአት በትዊተር ገጹ የመከላከያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ በኢትዮጵያ ከእንግሊዝ አምባሳደር አሊስተር ሚሲፔል ጋር ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ የወጣው ዘገባ እውነታውን ሙሉ ለሙሉ የማያንጸባርቅ መሆኑን መግለጹን ተከትሎ ነው።

እንደ ኤምባሲው ከሆነ አምባሳደሩ ከጀኔራል ብርሃኑ ጁላ ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ በትግራይ ክልል ያለው ግጭት እንደሚያሳስባቸው የተናገሩ ሲሆን፣ ጨምረውም ለግጭቱ ፖለቲካዎች መፍትሔ እንዲበጅለት እንዲሁም የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ መሬት ላይ እንዲወጡ አስገንዝበዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img