Sunday, October 6, 2024
spot_img

የአማራ ፖለቲካ ፓርቲዎች የተሰኘው ምክር ቤት መቋቋምን በተመለከተ ጥሪ እንዳልተደረገለት አብን አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሚያዝያ 21፣ 2013 ― በተያዘው ሳምንት ገዢው ብልጽግና ፓርቲን ጨምሮ ስምንት የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎችን ያቀፈ የአማራ ፖለቲካ ፓርቲዎች የተባለ ምክር ቤት ቢቋቋምም በክልሉ የሚንቀሳቀሰውና ሰፊ ማኅበራዊ መሠረት እንዳለው የሚናገረው አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ጥሪ እንዳልተደረገለት አስታውቋል፡፡

አዲሱ ምክር ቤት ከዚህ ቀደም ገዢው ፓርቲ በበላይነትና በብቸኝነት መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ሲያሳልፍ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ግን ስለ ክልሉ ይገደናል የሚሉ ፓርቲዎች በሙሉ መሳተፍ እንዲችሉ የተቋቋመ መሆኑን የአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዲሀን) ሊቀመንበርና የምክር ቤቱ ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አለምነህ ለአሐዱ ራድዮ ተናግረዋል፡፡

ነገር ግን እርሳቸው ይህን ቢሉም በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በምክር ቤቱ ውስጥ አለመካተቱ የተነገረ ሲሆን፣ ይህንኑ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ዩሱፍ ኢብራሂም አረጋግጠዋል ነው የተባለው፡፡

በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሰጡት የምክር ቤቱ ኃላፊ በበኩላቸው፣ እርሳቸው ምክር ቤቱን ከመምራት ባለፈ ለፓርቲዎች ጥሪ የማድረግ ስልጣን እንደሌላቸው በመግለጽ፣ ይህን ሥራ በበላይነት የመራው የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የክልሉ ቅርንጫፍ መሆኑንም አክለዋል፡፡

ከአማራ ብሐየራዊ ንቅናቄ ጋር በተገናኘ ሌላ መረጃ የንቅናቄው ሊቀመንበር የፌስቡክ አካውንት ከቁጥጥራቸው መውጣቱን የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ዩሱፍ ኢብራሂም ገልጸዋል፡፡

‹‹የግብር ከፋዩ ገንዘብና ተቋማት ሕዝቡን ለማጥቃት ማገልገላቸው ቀጥሏል›› ያሉት ምክትል ሊቀመንበሩ፣ ‹‹ሰሞኑን በቤትና በቢሮዎች አካባቢ የሚታየው የደኅንነት ወከባ የመልእክትና የግንኙነት መስመሮችን ወደ መተላለፍ ተሸጋግሯል›› ሲሉም አስፍረዋል፡፡

ገዢው ብልጽግና ፓርቲ ከሰሞኑ በአማራ ክልል ለተካሄዱ መንግሥትን የተቃወሙ ሠልፎችን በማስተባበር የአማራ ብሔራዌ ንቅናቄን መክሰሱ የሚታወስ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img