አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሚያዝያ 21፣ 2013 ― ግብጻዊያኑ እየሩሳሌም በሚገኘው ጎለጎታ ገዳም በኢትዮጵያውያን ይዞታ ላይ ወረራውን ፈጽመዋል የተባለው ትላንት ረቡዕ ሌሊት ለዛሬ አጥቢያ መሆኑ ነው የተሰማው፡፡
ግብጻዊያኑ በፈጸሙት የይዞታ ወረራ ሰበብ ከፍተኛ ብጥብጥ ፈጥረው ነበር የተባለ ሲሆን፣ በሥፍራው ተሰቅሎ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ አውርዱ ማለታቸውንም የወጡ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡
ችግሩ መፈጠሩን ተከትሎ የእስራኤል የሀገር ውስጥ ምክትል የደኅንነት ሚኒስትር የሆኑት ትውልደ ኢትዮጵያዊው ጋዲ ይቫርከን ግብጻዊያኑ ጥሰው ገብተው ወረውታል የተባለውን የኢትዮጵያውያን ይዞታ በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ ማድረጋቸው ተነግሯል፡፡
የአገሪቱ የሀገር ውስጥ ምክትል የደኅንነት ሚኒስትር ጋዲ ይቫርከን ከዚህ ክስተት ቀድሞም ከኢትዮጵያ ጋር በተገናኙ ጉዳዮች ንቁ ተሳትፎ ያላቸው መሆኑ ተነግሮላቸዋል፡