Friday, November 22, 2024
spot_img

አሊ በርኬ የቤት ሥጦታ ተበረከተላቸው

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሚያዝያ 21፣ 2013 ― በካራማራ ጦርነት የዚያድባሬን ታንኮች በእጅ ቦንብ እንዳጋዩ የሚነገርላቸው ሻለቃ ባሻ አሊ በርኬ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤት እንደሰጣቸው ተሰምቷል።

በዛሬው ዕለት የከተማ አስተዳደሩ ከ15 ዓመታቸው ጀምሮ ለሀገራቸው ነጻነት ለተዋደቁት የክብር ኒሻን ተሸላሚው ጀግና ሻለቃ ባሻ አሊ በርኬ የቤት ስጦታ ማበርከቱን ከአዲስ አበባ ፕርስ ሴክሬተሪያት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በአንድ ወቅት በሀገሪቱ ከሚታተሙ ጋዜጣ ጋር ባደረጉተ ቃለ ምልልስ ‹‹ጡረታዬ አልተከበረልኝም ጡረታዬ ቢከበርልኝ በእዚህ እድሜዬ ኩንታል እሸከም ነበር? አገሬ ለከፈልኩት ውለታ ፊት ነስታኛለች ጡረታ እኮ የለኝም›› ብለው ነበር።

ሻለቃው ‹‹አሊ በርኪ ጐታ ኦሮሞ›› (አሊ በርኪ የኦሮሞ ጀግና) የተሰኘ የሻለቃ ባሻ አሊ በርኬን ሕይወት የሚያስቃኝ መጽሐፍ ተጽፎላቸዋል።

መጽሐፉ በ1969 እና 1970 በኢትዮጵያና በሶማሊያ መካከል በተደረገው ጦርነት ወቅት ከፍተኛ ተጋድሎ የፈጸሙበትን ታሪክ የሚዳስስ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img