Monday, September 23, 2024
spot_img

በአጣዬ አካባቢ በተከሰተው ችግር የአገር ውስጥና የውጭ አካላት እጅ እንዳለበት የአካባቢው ኮማንድ ፖስቱ አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሚያዝያ 21፣ 2013 ― በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ እና የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞኖች በቅርቡ ከተፈጠረው ችግር ጀርባ የተለያዩ የአገር ውስጥና የውጭ አካላት፣ የፖለቲካ ድርጅቶችና የመንግሥት መዋቅር እጅ እንዳለበት መታወቁንና በቀጣይ በማስረጃ የተደገፉ መረጃዎች የማሰባሰብ ሥራ እንደሚሰራ በአካባቢው የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት አስተባባሪ ሌተናል ጄኔራል ደስታ አቢቼ ነግረውኛል ብሎ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ሌተናል ጄኔራል ደስታ አቢቼ በተፈጠረው ችግር አሉበት ያሏቸው የአገር ውስጥ እና የውጭ አካላት እነማን እንደሆኑ የሠጡት ፍንጭ ስለመኖሩ የተጠቀሰ ነገር የለም፡፡

አስተባባሪው፣ ኮማንድ ፖስቱ ግዳጅ ከተሰጠው ጀምሮ አካባቢው ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲመለስ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱንም ገልጸዋል ነው የተባለው፡፡

በተጨማሪም ግጭትና ጸብ አጫሪነትን እንዲሁም መንገድ መዝጋትን በማስቆም የተቋረጡ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና አስተዳደራዊ ሥራዎች እንዲጀመሩ የማድረግ ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝም በዘገባው ተመላክቷል፡፡

አካባቢው የተረጋጋ እንቅስቃሴ እየታየበት መሆኑን ተከትሎም ተቋርጠው የነበሩ የትራንስፖርት አገልግሎቶችና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን፣ የተቋረጡ የስልክ፣ የውሃና የኤሌክትሪክ አገልግሎቶችም ዳግም ተጀምረዋል ተብሏል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img