Sunday, September 22, 2024
spot_img

በአብዬ በሰላም ማስከበር የነበሩ 100 ያህል የትግራይ ተወላጅ ወታደሮች ወደ ኢትዮጵያ መመለስ አንፈልግም ማለታቸው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሚያዝያ 21፣ 2013 ― በተባበሩት መንግሥታት የሰላም አስከባሪ ውስጥ በሱዳን አብዬ ግዛት በተልእኮ ላይ የነበሩ 100 ያህል የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ወታደሮች ወደ አገራችን አንመለስም ማለታቸውን ሱዳን ትሪቡን ምንጮቼ ነግረውኛል ብሎ ዘግቧል፡፡

ወታደሮቹ ከተልእኳቸው በሰሜናዊ ዳርፉር ኤል ፋሸር የተባለች ከተማ ከደረሱ በኋላ ነው ወደ ኢትዮጵያ አንመለስም ማለታቸው የተሰማው፡፡ እነዚህ ወታደሮቹ ወደ አገር ቤት አንመለስም ለማለታቸው ምክንያት አድርገው ያቀረቡት አሁን በፌዴራል መንግሥት እና በሕወሃት መካከል ያለውን ግጭት ተከትሎ ችግር ውስጥ እንገባለን በሚል ፍርሐት መሆኑም ተነግሯል፡፡

የወታደሮቹን ውሳኔ በተመለከተ የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መርየም አል መሕዲ ከደቡብ ሱዳን አቻቸው ጋር በትላንትናው እለት መምከራቸውን ዘገባው ጠቁሟል፡፡

ጉዳዩን አስመልክቶ በኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት በኩል የተባለ ነገር ስለመኖሩ የተጠቀሰ ነገር የለም፡፡ እንደ ተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ ከሆነ ሰሜን ሱዳን እና ደቡብ ሱዳንን በሚያዋስነው በአብዬ ግዛት 3 ሺሕ 300 ያህል የኢትዮጵያ ወታደሮች ይገኛሉ፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img