Sunday, September 22, 2024
spot_img

የሶማሊያው ፕሬዚዳንት የሥልጣን ዘመን የማራዘም እቅዳቸውን ትቼዋለሁ አሉ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሚያዝያ 20፣ 2013 ― የሶማሊያው ፕሬዚዳንት መሐመድ ዐብዱላሂ ፋርማጆ ለሁለት ዓመታት የተራዘመ የሥልጣን ዘመናቸውን በመሰረዝ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ ማቅረባቸው ተነግሯል፡፡

ፋርማጆ ይህን ከማለታቸው ሰአታት ቀድሞም የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር መሐመድ ሑሴን ሮብሌ የፕሬዝዳንቱን የሥልጣን ማራዘም እቅድ በማውገዝ አገሪቱ ለአዲስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዝግጅት ማድረግ እንደሚኖርባት መግለጻቸውን ሬውተርስ ዘግቧል።

በሶማሊያ ከሰሞኑ ከተራዘመው የፕሬዚዳንቱ የሥልጣን ዘመን ጋር ተያይዞ የእርሳቸው ደጋፊዎችና ታቃወሚዎች ጎራ ለይተው ግጭት ውስጥ ገብተው እንደነበር ከአገሪቱ የሚወጡ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ ግጭቱን ተከትሎም ነዋሪዎች ቀያቸውን በመልቀቅ እየሸሹ እንደነበር ነው የተገለጸው፡፡

ፕሬዚዳንቱ ዛሬ ለሃገሪቱ ሕዝብ ባደረጉት ንግግር በሀገሪቱ ምርጫ እንዲካሄድ የወሰኑ ሲሆን፣ የስልጣን ዘመኑን መራዘም የተቃወሙትን ጠቅላይ ሚኒስትርም አድንቀዋል፡፡

በሶማሊያ በአሁኑ ወቅት የገባችበትን ፖለቲካዊ ችግር ተከትሎ በርካቶች አልሻባብ በሀገሪቱ የተፈጠረውን ክፍተት በመጠቀም ችግር ይፈጥራል በሚል ስጋታቸውን እየገለጹ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img