Monday, September 23, 2024
spot_img

አቶ ጌታቸው ረዳ ሕወሃት የሰሜን እዝን አጥቅቷል መባሉን ካዱ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሚያዝያ 20፣ 2013 ― ሕወሃት በጥቅምት የመጨረሻ ቀናት በአገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን እዝ ላይ ጥቃት አድርሷል መባሉን ከመንግሥት ጋር ውጊያ ውስጥ እንደሚገኙ የሚናገሩት አመራሩ አቶ ጌታቸው ረዳ ክደዋል፡፡

አቶ ጌታቸው ይህን ያሉት ትግራይ ሚዲያ ሐውስ በተባለ የኦንላይን ሚዲያ በተሠራጨ በምስል የተደገፈ ቆይታቸው ወቅት ነው፡፡ ‹‹የሰሜን እዝን አጥቅተዋል የሚል ተደጋጋሚ ተረት ስለተፈጠረ እውነት የሚመስለው ሰው አለ›› ያሉት አቶ ጌታቸው፣ ‹‹ሰሜን እዝን ያጠቃነው ነገር የለም›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

አክለውም ‹‹የሰሜን እዝ ተጠቃ ከተባለበት ከሦስት እና አራት ቀን በፊት ዐቢይ ከመላው ኢትዮጵያ ሠራዊት እያስገባ ነበር›› ብለዋል፡፡

አቶ ጌታቸው ይህን ቢሉም በዚሁ ጦርነት የሞቱት ሌላኛው የሕወሃት ሰው አቶ ሴኩቱሬ ጌታቸው ከዚህ ቀደም በሰሜን እዝ ላይ ‹‹መብረቃዊ እርምጃ›› እንደተወሰደበት የሕወሃት ልሳን በሆነው በድምጺ ወያኔ ቴሌቪዥን ቀርበው አረጋግጠው ነበር፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በብሔራዊ ቴሌቪዥን ቀርበው ‹‹ከሃዲ ኢትዮጵያውያን፣ ኢትዮጵያን ወግተዋታል›› በማለት በሕወሃት ላይ የሚወሰደው እርምጃ መጀመሩን ይፋ ያደረጉት ጥቅምት 24፣ 2013 እኩለ ሌሊት ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img