Monday, September 23, 2024
spot_img

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፉን የኮቪድ 19 የይለፍ መተግበሪያን በመጠቀም ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆነ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሚያዝያ 20፣ 2013 ― የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፉን የኮሮና ቫይረስ የይለፍ መተግበሪያ በመጠቀም ከአፍሪካ የመጀመርያው መሆኑን አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ በድረ ገጹ ላይ እንዳስታወቀው በዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር (አያታ) የተዘጋጀውን የዲጂታል የይለፍ መተግበሪያን በመቀበል በአፍሪካ ካሉ አየር መንገዶች የመጀመርያው ሆኗል።

የኮሮና ቫይረስ ውጤትን ብሎም የክትባት ሁኔታን ለመለየት እንደሚያግዝ የተነገረለት ይህ መተግበሪያ፣ ተጓዦችን፣ አየር መንገዱን፣ ላቦራቶሪዎችን እንዲሁም መንግሥትን በማቆራኘት ትክክለኛ የኮሮና ቫይረስ የምርመራ ውጤት በጉዞ ወቅት መቅረቡን የሚያረጋግጥ ነው።

ይህም ተጓዦች የኮሮና ቫይረስ ውጤታቸውን እና የክትባት ማረጋገጫቸውን ቀድመው የሚያይዙበት ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይህንን የዲጂታል የይለፍ ሥርዓት በአራት የተለያዩ ዓለም አቀፍ በረራዎች ላይ ከሁለት ቀናት በፊት መተግበር እንደጀመረ ነው በድረ ገጹ ይፋ ያደረገው፡፡

አየር መንገዱ አክሎም ከአዲስ አበባ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ እና ቶሮንቶ እንዲሁም ከለንደን እና ከቶሮንቶ ወደ አዲስ አበባ የሚያደርጋቸው በረራዎች ላይ ሙከራውን እንደሚያካሂድ አስታውቋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img