Saturday, November 23, 2024
spot_img

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኤርትራ ወታደሮች በኦሮሚያ ክልል አሉ ስለመባሉ መረጃ የለኝም አለ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሰኔ 3፣ 2013 ― የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ አማባሳደር ዲና ሙፍቲ በዛሬው እለት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው ላይም የኤርትራ ወታደሮች በምእራብ ኦሮሚያ ውስጥ በሚገኙ ዞኖች እና በደቡብ ኦሮሚያ ውስጥ አሉ ስለሚባለው ጉዳይ ጥያቄ ቀርቦላቸው ‹‹መረጃ የለኝም›› የሚል ምላሽ መስተታችን አል ዓይን ዘግቧል፡፡

ከሰሞኑ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የኤርትራ ወታደሮች በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ውስጥ አሉ በሚል ሲነገር መሰንበቱ ይታወሳል፡፡

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ላይ ከ5 ቀናት በፊት ባወጣው መረጃ የኤርትራ ወታደሮች በኦሮሚያ ክልል በተለይም በቦረና ዞን ነጌሌ ከተማ አካባቢ እንዲሁም በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አባይ ጮመን በሚባል ስፍራ መታየታቸውን አስታውቋል።

ኦነግ የኤርትራ ወታደሮች ናቸው ያላቸው ግለሰቦች ‹‹ሁሉም አፋን ኦሮሞ ቋንቋን የማይችሉ እና የተወሰኑት ብቻ አማርኛ ቋንቋ የሚችሉ ናቸው›› ብሏል።

ይሁንና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቱ ‹‹የኤርትራ ወታደሮች በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ታይተዋል ስለመባሉ ምንም መረጃ የለኝም›› ብለዋል።

አማባሳደር ዲና አክለውም የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል መውጣት መጀመራቸውን ገልጸው፣ ይህንንም መከላከያ ሚኒስቴር ማረጋገጡንም አመልክተዋል፡፡

ሆኖመ አምባሳደሩ በትግራይ ክልል ከሚገኙ የኤርትራ ወታደሮች ምን ያክሉ እንደወጡና ቀሪዎቹ መቼ ሙሉ በሙሉ ይወጣሉ የሚለውን በተመለከተ የተሟለ መረጃ እንደሌላቸው ነው የገለጹት፡፡ ሙሉ መረጃ የለኝም” ሲሉ መልሰዋል።

በሌለ በኩል የሰሜን አትላንቲክ ቃልኪዳን ጦር ኔቶ በትግራይ ክልል ካለው ችግር ጋር በተያያዘ ‹‹ኢትዮጵያን ለመውረር ተዘጋጅቷል›› በሚለው ላይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መረጃ እንደሌለው በመጠቆም፤ ‹‹ኢትዮጵያ ከሁሉም የኔቶ አባላት ጋር መልካም ግንኙነት ነው ያላት፤ ይህንን ያደርጋሉ የሚል እምነት የለኝም›› በሚል የራሳቸውን አስተያየት ሰጥተዋል።

ከትግረይ ክልል ጋር በተገናኘ ‹‹350 ሺሕ ሰዎች ለረሃብ ተጋልጠዋል›› በሚል ይፋ ያልሆነ የተባበሩት መንግስታት ጥናትን ዋቢ በማድረግ የወጣው መረጃ ትክክል እንዳልሆነ አምባሳደር ዲና አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ‹‹ረሃብ ተከስቷል ለማለት የተቀመጡ መስፈርቶች አሉ፤ አሁን በትግራይ ባለው ሁኔታ ከ90 በመቶ በላይ የክልሉ ነዋሪ ሰብዓዊ ድጋፍ አግኝቷል›› ሲሉ መልሰዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img