Saturday, November 23, 2024
spot_img

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሽዴን ወደ ሶማሊያ ሊልኩ መሆኑ ተሰማ

አምባ ዲጂታል፤ ቅዳሜ ጥር 18፣ 2016 – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ የሚመሩትን ልኡክ ወደ ሶማሊያ የሚልኩት በቅርብ ሳምንታት ከባሕር በር ስምምነት ጋር በተገናኘ የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ መሆኑ ተነግሯል፡፡

አሕመድ ሽዴ የሚመሩት ልኡክ ወደ ሶማሊያ የሚያቀናበት ቀን ባይታወቅም፤ ወደ ሶማሊያ በማቅናት ኢትዮጵያ ከሶማሊላነድ ጋር የተፈራረመችውን የባህር በር የመግባቢያ ስምምነት ተከትሎ ያኮረፈችው ሶማሊያን የማግባባት ስራ ይሠራሩ እንደሚሠሩ ዋዜማ በድረ ገጹ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ ከሦስት ሳምንታት በፊት ይፋ ባደረጉት ስምምነት ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ የባሕር ጠረፍ በማግኘት፤ በምትኩ ሶማሊያ እንደ አንድ ግዛቷ ለምትመለከታት ሶማሊላንድ የአገርነት ዕውቅናን እንደምትሰጥ መገሩ ይታወሳል፡፡ ይህ ስምምነት ይፋ ከተደረገ በኋላ ሐሰን ሸይኽ ማሕሙድ የሚመሯት ሶማሊያ በባለሥልጣኖቿ በኩል ቁጣዋን ስታሰማ ሰንብታለች፡፡ ሶማሊያ ስምምነቱ በሉዓላዊነቷ ላይ የተፈጸመ ጥቃት መሆኑን ገልጻለች፡፡

ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ ከሶማሊያ ተቃውሞ ቢሰማም የፈረሙትን የመግባቢያ ስምምነት በአንድ ወር ውስጥ ተግባራዊ እንደሚያደርጉ አሳውቀዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img