Saturday, November 23, 2024
spot_img

ወልቃይት እና ራያ በአማራ ክልል ሥር እንዲሆኑ እውቅና የማይሰጥ የግጭት ማቆም ስምምነት በአማራ ሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የለውም ሲሉ የፓርላማ አባሉ ተናገሩ

አምባ ዲጂታል፤ ዐርብ ጥቅምት 25 2015 ― አማራ እና ትግራይ ክልሎችን የሚያወዛግበው ወልቃይት እና ራያ በአማራ ክልል ሥር እንዲሆኑ እውቅና የማይሰጥ የግጭት ማቆም ስምምነት በአማራ ሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የለውም ሲሉ የተናገሩት የአብን ተመራጭ የፓርላማ አባሉ ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ናቸው፡፡

ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ይህን የተናገሩት ከፌዴራል መንግስቱ እና ሕወሓት የደቡብ አፍሪካ የሰላም ንግግር በኋላ ለሬውተርስ የዜና ወኪል ነው፡፡ የፓርላማ አባሉ ወልቃይት እና ራያ በአማራ ክልል ሥር እንዲሆኑ እውቅና የማይሰጥ የግጭት ማቆም ስምምነት ‹‹ዘላቂ ሰላም አያመጣም›› ሲሉም አክለዋል፡፡  

አሁን ስምምነቱን ዘላቂ ስምምነት አያመጣም ያሉት ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ፤ ከሳምንት በፊት ከቀድሞው የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ ጀነራል ተፈራ ማሞ፣ ከአቶ ቴዎድሮስ ትርፌ እና ከዶክተር ወንድወሰን አሰፋ ጋር ‹‹የአማራ ሕዝብ ተደራዳሪ ልዑክ›› የሚል ቡድን ማቋቋማቸውን አስታውቀው ነበር፡፡

የአማራ ማኅበር በአሜሪካ በወቅቱ ይፋ ባደረገው ደብዳቤ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት በሰላም ለመቋጨት በሚደረገው የሰላም ንግግር ሂደት የአማራ ሕዝብን ያገለለ መሆኑ እንደሚያሳስባቸው ገልጸው ነበር፡፡

ረቡዕ ጥቅምት 23፣ 2015 በተደረገው የሰላም ንግግር በፌዴራል መንግሥቱ እና በሕወሓት ተወካዮች መካከል የሰላም ስምምነት ፊርማ ተከናውኗል፡፡ ከፊርማው በኋላ ትላንት ጥቅምት 24፣ 2015 በአርባ ምንጭ ስታድየም ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሰሜን ኢትዮጵያ የይገባኛል ጥያቄ የሚነሳባቸው ቦታዎች ‹‹በሀገሪቱ ህግ ብቻ ምላሽ›› እንደሚያገኙ ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹‹በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የይገባኛል ጥያቄ የሚነሳባቸው እና አከራካሪ የሆነ ቦታዎች፤ ዳግም የሰው ልጆችን ህይወት ሳይነጥቁ፤ በሰላም፣ በድርድር እና በሀገሪቱ ሕገ መንግስት መሰረት ብቻ ምላሽ እንዲያገኙ በሁለቱም ወገኖች ከመተማመን ተደርሷል›› ሲሉ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img