Saturday, November 23, 2024
spot_img

የአሜሪካው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ በአዲስ አበባ ከመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ተወያዩ

አምባ ዲጂታል፤ ዐርብ ጥቅምት 4 2015 ― የአሜሪካው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ አምባሳደር ማይክ ሐመር በአዲስ አበባ ከተማ ተገኝተው ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር ተወያይተዋል፡፡

የአምባሳደር ማይክ ሐመር ማይክ ሐመር አዲስ አበባ መግባታቸው የተሰማው ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በአፍሪካ ኅብረት አሸማጋይነት በደቡብ አፍሪካ ይካሄዳል ተብሎ እቅድ ተይዞለት ሳይካሄድ ከቀረው የፌዴራል መንግሥት እና ሕወሓት የሰላም ንግግር በኋላ ነው፡፡

ማይክ ሐመር በሰሜን ኢትዮጵያ ላለው ጦርነት የሚደረገውን የሰላም ጥረት ለመደገፍ በሚል ወደ ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ኢትዮጵያ ጉዞ መጀመራቸው መነገሩ አይዘነጋም፡፡ ይኸው ንግግር ሳይሳካ መቅረቱን ተከትሎ ከኬንያ እና ደቡብ አፍሪካ ጉዟቸው በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ያቀኑት ሐመር፤ ከአቶ ደመቀ መኮንን ጋር ባደረጉት ውይይት ይኸው የሰሜን ኢትዮጵያው ጉዳዳ መነሳቱን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ውጪ ጉዳይ በመረጃው አቶ ደመቀ ከልዩ መልዕክተኛው ማይክ ሐመር ጋር ባደረጉት ውይይት መንግስት ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል ያለ ሲሆን፣ ሐመር በበኩላቸው አሜሪካ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ለሚካሄደው የሰላም ውይይት ድጋፏን አጠናክራ ትቀጥላለች ማለታቸውንም አስነብቧል፡፡

የአፍሪካ ህብረት ይመራዋል ተብሎ የነበረውና በደቡብ አፍሪካ ታቅዶ የነበረውን የሰላም ንግግር የአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፣ የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና በቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፉምዚሌ ምላምቦ እንደሚመራ ይመራል ቢባልም፤ በሎጂስቲክስ አለመሟላት ምክንያት መራዘሙ ነው የተገለጸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከአደራዳሪዎቹ መካከል የሆኑት ኡሁሩ ኬንያታ በተያዘው ቀን መገኘት አልችልም መለታቸውም ይታወሳል፡፡

በፌዴራል መንግሥት እና በሕወሓት መካከል የሚካሄደው ጦርነት በተያዘው ጥቅምት ወር መጨረሻ ሁለት ዓመት ይደፍናል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img