Sunday, November 24, 2024
spot_img

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛው ዴቪድ ሳተርፊልድ ኃላፊነታቸውን ሊለቁ ነው

  • መልዕክተኛው በዛሬው እለት ከምክትላቸው ጋር አዲስ አበባ እንደሚገቡ የአገራቸው የውጭ ጉዳ መስሪያ ቤት አስታውቋል

አምባ ዲጂታል፤ ረቡዕ ሚያዝያ 5 2014 በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ገደማ የቀድሞውን የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማንን ተክተው ላለፉት ጥቂት ወራት ሲሠሩ የቆዩት አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ሥልጣናቸውን ሊቀቁ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ፎሬን ፖሊሲ ይዞት የወጣው ዘገባ እንደሚያመለክተው፤ ሳተርፊልድን በመተካት በጊዜያዊነት ቦታውን ምክትላቸው ፓይተን ኖፍ ይረከባሉ፡፡

ነገር ግን ሳተርፊልድ ጥቂት ወራት ብቻ የቆዩበትን ኃላፊነት ለምን እንደሚለቁ የታወቀ ነገር ስለመኖሩ ዘገባው አላሰፈረም፡፡

በሌላ በኩል እኚሁ የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ እና ቦታቸውን ይረከባሉ ተብለው የሚጠበቀው ምክትላቸው ፓይተን ኖፍ በዛሬው እለት አዲስ አበባ እንደሚገቡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛው እና ምክትላቸው በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት ባለሥልጣናት፣ ከሰብአዊ ድርጅቶች ተወካዮች እንዲሁም ከዲፕሎማቲክ አጋሮች ጋር ይነጋገራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ መግለጫ ያመለክታል፡፡

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው፤ የአምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ እና የምክትላቸው ፓይተን ኖፍ የኢትዮጵያ ጉብኝት ግጭት ለማቆም፣ ያልተገደበ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እንዲኖር፣ ተፈጽመዋል የተባሉ የመብት ጥሰቶች ግልጽ ምርመራ እንዲደረግ እና ለግጭት በድርድር መፍትሄ ለመስጠት አሜሪካ የምታደርገው ጥረት አካል ነው ብሏል።

ልዩ መልዕክተኛው አምባሳደር ሳተርፊልድ በቆይታቸው ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት፣ ከአፍሪካ ኅብረት እና ከተባበሩት መንግሥታት ተወካዮች እና ከሰብአዊ ድርጅት አስተባባሪዎች ጋር ይገናኛሉ ሲል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አስታውቋል።

አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ በቅርቡ ማለትም መጋቢት 12 እና 13፣ 2014 አዲስ አበባ ተገኝተው ለሁለት ቀናት አድርገው ነበር።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img